በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች
የመጀመሪያ ዙር ከመስከረም 19 እስከ 30 2007 ዓ/ም ሁለተኛ
ዙር ከጥቅምት 3 እስከ 14 2007 ዓ/ም ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የገለፀው መረጃው። የስብሰባው አጀንዳም የተሃድሶ መስመራችንና
የኢህ.አ.ዴ.ግ የህዳሴ ጉዞ በማለት የቀረበ ሲሆን በሰራተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያገጠመው መሆኑን አስረድቷል፣
በተለይ በአዲስ አበባ በፕላዝማ የተደገፈ በምክትል ከንቲባውና በፖለቲካ አማካሪው አቶ ተወልደ እየተመራ ባለው ስብሰባ፥
ተሰብሳቢዎች ፀረ ዲሞክራሲ የሆነ አካሄድ ለሚከተለው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በርካታ ጥያቄዎች እንዳነሱ ተገልጿል፣
- ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ
ያህል ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ያለፉትን ስርዓቶች ድክመት መኮነን ብቻ እንጂ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል በብሄሮች መካከል የፈጠረውን
ጥላቻ ለምን አያነሳም?
- የገዥውን መንግስት ጉድለት የሚናገሩ ተቃዋሚወች
ለምን ፀረ ልማት እየተባሉ ይታሰራሉ?-
- በሃይማኖትና በብሄር የሚነሱ ግጭቶችን ለምን
የተቃዋሚወች ችግር ይባላል?
- አንድ ድርጂት ለበርካታ ጊዜ በስልጣን ላይ መቆየት ለሃገር የሚያመጣው ለውጥ የለም ኢ.ህ,አ.ዴ.ግ በዲሞክራሲ
ስለማያምን የተቃዋሚ አመራሮች እየታሰሩ ናቸው እና ሌሎችም ጥያቄዎች መነሳታቸውን ለማወቅ ተችሏል፣