Wednesday, October 22, 2014

በዚህ ሳምንት ለህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በመቃወም በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ ድርጅት ተቀላቀሉ፣




ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጅት ከተቀላቀሉት የተወሰኑትን ለመጥቀስ።-
·        ዕንድዊ ይህደጎ ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቀበሌ ማይሓማቶ
·        ሽሻይ ተስፋጋብርና ሽዊት ገብረሂወት ከምስራቅ ዞን ጉሎ መኸዳ ወረዳ ማርታ ቀበሌ
·        ሚለን ስልጣንና አባዲ ይህደጎ ከሰሜናዊ ምዕራብ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ  ዓዲ ክልተ ቀበሌ
·        እንድርያስ ገብረመስቀልና መኣዛ አብረሃ ከምስራቅ ዞን ጉሎ መኸዳ ወረዳ ቀበሌ ዛላምበሳ
·        ጉዕሽ ተስፋ ማርያም ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ  በሪሃ ቀበሌ
·        ዕቡይ ተኽሎም ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዲ ዓንበራይ ቀበሌ
·        ሓየሎም ነጋሲና መሓሪ ባራኺ ከማዕከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ  ሆያ ቀበሌ
·        ዕቑባይ አለም ከምስራቃዊ ዞን ጉሎ መኸዳ ወረዳ  ቅልዓት ቀበሌ ሲሆኑ።
   እነዚህ ወጣቶች ወደ ትህዴን እንዲመጡና እንዲታገሉ ያስገደዳቸውን ዋነኛ ምክንያት ሲገልፁ፤ በሃገራችን ባለው ከፋፋይ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ምክንያት፤ በሃገራችን እንዳንኖርና ሰርተን እንዳንበላ እንቅፋት ስለሆነብን፥ ለዚህ ኢትዮጵያን ለማይወክል ስርዓት ለማስወገድ፥ ከጊዜ ወደጊዜ ቀልጣፋ እድገት እያሳየ ካለው ህዝባዊ ድርጅት ጋር ተቀላቅለን የበኩልችንን ለማበርከትና የትጥቅ ትግል ለማካሄድ በረሃ ወጥተናል ሲሉ ወጥቶቹ ገለፀዋል፣
    በተለይም  ወጣት ዕቑባይ አለም አሁን ባለንበት ወቅት በሃገራችን ውስጥ ያሉ ወጣቶች በስራ እጦት ምክንያት በከባድ ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ፤ በዚህ የተነሳም ብዛት ያላቸው የሃገራችን ወጣቶች ሃገራቸውን እየለቀቁ ዋስትና በሌለው መንገድ ወደ አረብ ሃገሮች በሚሄዱበት ሰዓት በርካታ ወጣቶች ውቅያኖስ ውስጥ ጠልቀው እንደሚቀሩና አንዳንዶቹ ደግሞ በየበረሃው በውሃና በምግብ እጦት ምክንያት እያለቁ ይገኛሉ በማለት፤ እሱም ትምህርት ጨርሰው ስራ ካጡ የሃገራችን ወጣቶች መካከል አንዱ እንደሆነና ለቤተሰቡም ሸክም ሆኖ እንደነበር በመግለፅ። ስራ ለመቀጠር በምትሻበት ሰዓትም በዘመድ አዝማድና በጉቦ ስለሆነ ብዙ የሃገራችን የድሃ ልጅ ስራ ማግኘት እንደማይችሉ ገልጿል፣
     ወጣት እንድሪያስ ገብረመስቀል በበኩሉ የመንግስት ሰራተኛ እንደነበረና ግን ደግሞ የተቋሙ ሃላፊዎች የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በነፃነት ሊያሰሩት ስላልቻሉ መብቱን ለማስከበር ትግል እንደመረጠ አክሎ አስርድቷል፣