እነዚህ በዓብይ ዓዲና ሃውዜን ከተሞች የሚገኙ በማስተር ፕላን ስም እንዲፈርሱ የተወሰነባቸው መኖሪያ ቤቶች
ካሳ የሚሆን ክፍያ ለመክፈል ለባለቤቶች ከ500 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ለቤት መስሪያ የሚውል መሬት ሊሰጣቸው መሆኑ በስርዓቱ
ካድሬዎች የተገለፀላቸው ቢሆንም። በተግባር ግን በጉቦና በአድሎ እየተፈፀመ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአስተዳዳሪዎች
ጉቦ መክፈል ያልቻሉ 200 ሺህ ብር ብቻ ሲከፈሉ ጉቦ ለከፈሉት ግን ከ500 ሺህ ኣስከ 600 ሺህ ብር ካሳ ከተከፈሉ በኋላ በአግባቡ ያልተከፈሉ ወገኖች ግን ይህ አካሄድ
ትክክልና ፍትሃዊ ስላልሆነ ቤታችንን አናፈርስም በማለት ተቃውሞ እያካሄዱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣