እንደምንጮቻችን መረጃ በአንከሻ ወረዳ ዳዲ ደንገሶም ተብሎ በሚጠራው አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት ገንዘብ ያዥ በመሆን ይሰራ የነበረ ከክልል የተላከ መምህር በሃላፊነት እንዲይዘው የተረከበውን የትምህርት ቤት ገንዘብ
20 ሺህ ብር በላይ ያለምንም ምክንያት ሊያጠፋፋው እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል፣
ይህን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ የተሰጠውን ሃላፊነት ተጠቅሞ የህዝብንና
የሃገርን ንብረት ለግል ያዋለ ግለሰብ በትክክል ስንት እንዳጠፋ በባለሞያወች ተመርምሮ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ባቀረቡት ጥያቄ
መሰረት የሂሳብ ባለሞያዎች ከ20 ሺህ ብር በላይ እንዳጠፋፋ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ/ም ለፀረ ሙስና ኮሚሽን አባላት የባለስልጣኑን ወንጀል በሰነድ አስደግፈው ቢያቀርቡም እስካሁን ግን ሙስና የፈፀመው ግለሰብ
በህግ ቁጥጥር ስር ባለመዋሉ የተነሳ የአካባቢው ማህበረሰብ በስርዓቱ ላይ
ምሬቱን እየገለፀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣