ከስፍራው የደርሰን መረጃ
እንደሚያመለክተው። በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ በረኽት አካባቢ የሚገኝ ሃላፊነቱ የመንግስት የሆነ ሰፊ የእርሻ መሬት
ያለምንም ምርት ሲባክን የታዘቡ ወጣቶች በየአመቱ ክረምት እየዘሩ ለብዙ ዘመናት ምርት ሲያመርቱበት እንደቆዩ ከገለፀ በኋላ፥ በአለፈው
ክረምትም ሰሊጥ መዘራታቸውን የተረዱ አስተዳዳሪዎች መሬቱ የመንግስት ነው በማለት ሲከለክሏቸው ወጣቶችም ከዚህ ውጭ ሌላ መሬት እንደሌለን
እያወቃችሁ ማዳበሪያ በግዴታ ከሰጣችሁን በኋላ ለምን ትከለክሉናላችሁ በማለት ለኪሳራ እንዳይጋለጡ አቤቱታ እያቀረቡ መሆናቸውን ለማወቅ
ተችሏል፣
የበረኸት አካባቢ አስተዳዳሪዎች ዘር ዘርተው የከረሙ ወጣቶችን ሰሊጥ እንዳይጭዱት
በማለት ጥቅምት 5/2007 ዓ/ም እንዳሰሯቸውና እነኝህ አስተዳዳሪዎችም ይህንን ተግባር የሚፈፅሙበት ዋና ምክንያት ሰሊጡ ጥሩ ፍሬ
ይዞ በማየታቸው ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በመፈለጋቸው ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፣
ከታሰሩት ወጣቶች ለመጥቀስ ያህል።- ሙላቱ አዳነ፤ ክፍላይ ክፍለ፤ አደራጀው
ገብረማሪያም እና ሌሎችም ለጊዜው ስማቸው ያልተጠቀሰ እንደሚገኝበት የተገኝው መረጃ አመልክቷል፣