እነዚህ የጉጅሌው
ኢህአደግ ፊደራል ፖሊስ አባላት በአንገረብ ወንዝ አከባቢ ከሲቪሎች
ወገኖቻችን ገንዘብ ለመዝረፍ ሲሉ ንፁሃን ዜጎቻችን በጥይት እየገደሉ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው፣ ገንዘብ በመዝረፍ ላይ ከተሰማሩት
የፌደራል ፖሊሶች መካከል አንዱን፥ ተዘራፊዎቹ በቢላዋ ወግተው ሲገድሉት፥ ሌላ መሽጎ የቆየው የፖሊስ አባል ደግሞ ለሃለቃ ገብረኪዳን
ተስፋይና አቶ መኮነን አብራሃለይ የተባሉት የሚገኙባቸው ሲቪሎች በጥይት ተኩሶው እንደገደሏቸው አስረድቷል፣
ይህ ከንፁሃን ዜጎቻችን በታጠቁት ፖሊሶች
ገንዘብ የመዝረፍ ተግባር በዚህ አከባቢ ብቻ ሳይሆን፥ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢ የሚካሄድ አስነዋሪ ተግባር ነው ሲሉ በአከባቢው
የሚገኙ ህብረተሰብ በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣