Friday, October 24, 2014

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ የሻይ ቤት ባለቤቶች የስኳር አቅርቦት በማጣታቸው የተነሳ የሚሰሩበትን ቁርስ ቤት ለመዝጋት መገደዳቸው ታውቋል፣


 
    በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚኖር ህዝብ በከተማዋ ከንቲባ መረሳ አታኽልቲ ጥቅምት 5/2007 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ የቁርስ ቤትና የሻይ ቤት ባለቤቶች እንዲሁም ስኳር የሚያስፈልጋቸው ተቋማት፤ ስኳር ከከተማዋ ጠፍቶ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም ይህን ችግር ተረድቶ መፍትሄ የሚሰጥ የመንግስት አካል ባለመኖሩ ምክንያት፤ የከተማዋ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳችሁን ተረከቡን እያሉ ምሬታቸውን በስብሰባው ላይ በግልፅ እንደተናገሩ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ፣
    መድረኩን ይመራው የነበረው የከተማዋ ከንቲባ አቶ መረሳ አታኽልቲ ለቀረበለት ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ስላልቻለና ባሳየው እብሪት የተናደዱ የስብሰባው ተሳታፊዎችም፤ በኑሮ-አቸው ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ችግር አምርረው እንደተናገሩት ለማወቅ ተችሏል፣