Sunday, October 26, 2014

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ የፌደራል ፖሊስና ደህንነት አባላት በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለሚያካሂዱ ድርጅቶች የተለያየ እንቅፋት እየፈጠሩ ሊያሰሯቸው እንዳልቻሉ ምንጮቻችን ከስፍራው ገለፁ፣





በምጮቻችን መረጃ መሰረት ገዢው የኢህአደግ ቡዱን በአድርቃይ፤ ዳባት፤ ደባርቅና ጭልጋ በሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ለሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጽህፈት ቤት እንዳይከፍቱና መሰብሰቢያ አደራሽ እንዳይከራዩ ተላላኪ ካድሬዎች እንደከለከሏቸው መረጃው የገለፀ ሲሆን፥ ከመስከረም 11/2007ዓ/ም ጀምሮ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነት ወደ ቦታው እንደተሰማሩና እያንዳንዳቸውም የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል እንቅፋት እየፈጠሩባቸው እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ የተቃዋሚ ድርጅት አባሎች እንዳይንቀሳቀሱ ከሚያደርጉት መካከል ሰለሙን የተባለ የፌደራል ፖሊስ አባልና ተከታዩቹ ሲሆኑ፥ በቴሌቬዥን መስኮት ከተቋዋሚ ድርጅቶች ጋር የ2007ዓ/ም ምርጫን አስመልክቶ ጥሩ መግባባት እንዳለ በስርአቱ እየተገለፀ ቢሆንም፥ በተግባር ግን አለመግባባት እንዳለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣