በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኝ ህብረተሰብ በፀጥታ አስካባሪ ሃይሎች ከባድ ግፍ እየወረደባቸው እንዳለ የገለጸው መረጃው የቀድሞው ታጋይ
ምክትል መቶ አለቃ አንባቸው ታየ የተባለው ዜጋ፤ በቤተሰቡና በንፁሃን ዜጎች ላይ ግፍ እየፈፀመና እያስፈጸመ የነበረውን አቶ መንበረ ማህደር የተባለ የዞኑ የፀጥታ ሃላፊ፤ በዝምታ ሊያልፈው
ስላልቻለ ጥቅምት 1/2007ዓ/ም በጥይት እንደገደለው ታውቋል፣
አምባቸው ታየ ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ
ራሱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ እጁን በመስጠት ቤተሰቤንና ህዝቤን ከህግ ውጭ ሲያሰቃይ እያየሁት ዝም ማለት ሳልቻልኩኝ የራሴን እርምጃ
ወስጃለሁ ሲል ቃሉን እንደሰጠ የገለፀው መረጃው፤ በህዝቦች ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ በግንቦት ወር 2007ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ
ላይ የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ እንዳያስነሳ ከወዲሁ ክትትልና ቁጥጥር እየተካሄደባቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፣