Friday, November 7, 2014

የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ አስተዳዳሪዎች ወደ መረብ ወንዝ ወርዳችኋል በማለት ሰዎችን በማፈን ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ተገለፀ፣




     እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዓዲ ሃገራይና አከባቢው የሚኖሩ ወገኖቻችን ማህበራዊ ህይወታቸውን ለመምራት ሲሉ በሚንቀሳቀሱበት ግዜ፤ የጉጅሌው ህወሓት ኢህአዴግ ካድሬዎች ደግሞ እናንተ ቤታችሁ ትታችሁ ወደ መረብ ወንዝ የምትሄዱት ከተቋዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመገናኘት ብላችሁ ነው በማለት ሰዎችን እያፈኑ በመውሰድ ላይ እንዳሉ ታወቀ፣
   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው እንደዚህ አይነት ፀረ ህዝብ ተግባር በዞኑ በሰፊው እንደሚከሰት ከገለፀ በኋላ በዚህ ተግባርም ብርሃነ-መስቀል ሳህለ የተባለ የዓዲ ሃገራይ ነዋሪ የሚገኙባቸው ወገኖቻችን ጥቅምት 14 /2007 ዓ/ም ወዲ ቢተው በተባለ የፖሊስ አባል ታፍነው እንደተወሰዱ መረጃው አስታወቀ፣
   ባለፈው ሳምንትም በመደባይ ዛና ወረዳ የሚኖሩ ወጣቶች ወደ መረብ ወንዝ ሄዳችኋል በሚል ምክንያት በሰለኽላኻ ከተማ ታስረው እንዳሚገኙ በዜና እወጃችን መግለጻችን ይታወሳል፣