Friday, November 7, 2014

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ ዓዲ ኮኮብ አከባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ የወያኔ ኢህአደግ ወታደራዊ መኮንኖች እስርቤት ውስጥ ታጉረው እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገለፀ፣




    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በዓዲ ኮኮብ አከባቢ የሚገኘው የማዕከላዊ እዝ እስር ቤት በርከት ያሉ መኮንኖች የሚገኙባቸው የስርአቱ ወታደሮች ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው፤ በእስርቤቱ ታጉረው በመሰቃየት ካሉት መኮንኖች ውስጥ መ/አለቃ ተስፋይ አየነው የእዙ የመረጃ ሰብሳቢና ትንተና ሃላፊ፤ ተስፋይ ወዲ ራያ የእዙ መኮነን እስታፍ፤ አንድ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻለቃ መአርግ ያለው የአማራ ብሄር ተወላጅና ሌሎችም መሆናቸውን ከእስርቤቱ ውስጥ ሸልኮ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
   መረጃው በማከል ከታሰሩት መካከል አምሳ አለቃ ፍቃዱ ዳምጠው የተባለ ጥቅምት 14/ 2007 ዓ/ም ውሃ በጀሪካን አሸክመው እየወሰዱት በነበረበት ሰዓት ሊሮጥ ሞክሯል በሚል ምክንያት ተኩሰው እንደገደሉት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣