Friday, November 7, 2014

በቡሬ ግንባር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች የማያስፈሉጓቸው ሰዎችን ለማባረርና ለሚያስፈሉጓቸው ሰዎች ደግሞ ለማጠናከር ያለመ ሲያካይዱት የሰነበቱት ስብሰባ ያለ-ውጤት እንደተበተነ ተገለፀ፣




   ከቡሬ ግንባር የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በስብሰባው የተሳተፉት የ25ኛ ክፍለ ጦር አባላት፤ “እኛ እስከ አሁን ግዴታችንን እየፈፀምን ቆይተናል ስለዚህ ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ወደየ አከባቢያችን ስደዱን።” በማለት በስብሰባው ላይ በምሬት እንደተቃወሙ ከገለፀ በኋላ ስብሰባውን እየመራ የነበረው የክፈለ ጦሩ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል አሰፋ ቸኮል ደግሞ “አሁን የመሸኛ ግዜ አይደለም የተጨመረ ሰው ስለሌለ ሃገሪትዋን ለማን ትቷችኋት ልትሄዱ ነው።” ሲል በንዴት  የመለሰላቸው ሲሆን፤ በስብሰባው የነበረው ሰራዊት ደግሞ ግዴታችንን ፈፅመናል የጥያቄ መብታችን ይከበርልን በሚል ግርግር ስላነሱ፤ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉ ተገለጸ፣
    በግርግና ባለ-መረዳዳት ምክንያት የተቋረጠው ይህ ስብሰባ፤ ጥቅምት 12 2007 ዓ/ም እንዲቀጥል በሚል፤ ፍስሃ ኪዳነ የተባለው የግንባሩ አዛዥ ወደ ግንባሩ በመሄድ ከሃይል አዛዥ በላይ ስብሰባ ባካሄደበት ግዜ መኮንኖቹ ደግሞ በሰራዊቱ የተነሳው ተቃውሞ በመደገፋቸው ምክንያት የተጀመረው ስብሰባ ካለምንም ፍሬ እንደተበተነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣