በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ
የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆች ማህበራዊ ሂወታቸውን ለመምራት ሲሉ ወረዳቸውን
ትተው በሚንቀሳቀሱበት ግዜ፤ በስርአቱ ካድሬዎች እየታሰሩ እንዳሉ የገለፀው መረጃው ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ለመጥቀስ ያህል፦
·
ፍሱሕ ሓጎስ የአራዕ ቀበሌ ነዋሪ ከአዲ-ግራት፤
·
በርሀ ታዕሪፍ የወራዓትለ ነዋሪና ዮውሃንስ አለማ
የአሊቴና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ከሑመራ፤
·
ምስግና ዘገየ የዓሊቴና ቀበሌ ነዋሪ ከአማራ ክልልና
·
ወዲ ጎሚየ የተባለ ከሓራዛ ሰብዓታ ቀበሌ ነዋሪ
የሚገኙባቸው ከየሚሰሩበት አከባቢ ታስረው ወደ ኢሮብ ወረዳ እንደገቡ መረጃው ገለፀ፣
ከወረዳው ሳንወጣ በደውሃን ከተማ ከጥቅምት18
እስከ 24 2007 ዓ/ም ከቀበሌና ከወረዳ አስተዳዳሪዎች በላይ የተገኙበት ስብሰባ መወያያ ተብሎ የቀረበው አጀንዳ የሃሳብ ድጋፍ እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል፣
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በስብሰባው
እንደመነጋገርያ ተብለው ከቀረቡት ሃሳቦች መካከል ህገ-መንግስታችን እንዴት እየተተገበረ ነው? ማህበራዊ ፍትህ በህዝቡ ላይ እንዴት እየሄደ ነው? ለትህዴን እንዴት አድርገን ከህዝቡ እንነጥለው? በመጭው
ምርጫ ሙሉ በሙሉ ልንመረጥ እንችላለን ወይ? ወዘተ የሚሉ እንደሆኑና ከተሰብሳቢዎች ግን ምንም አጋዥ የሆነ ሃሳብ ባለመቅረቡ የተነሳ
ከክልል ስብሰባውን ለመምራት የመጡት ካድሬዎች የሚፈልጉትን እገዛ ሳያገኙ እንደተመለሱ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣