Saturday, November 15, 2014

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰብ ተከታዮች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ልዩነት ለፀረ ህዝብ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት እንዲቃወም ጥሪያቸውን አስተላለፉ፣




    በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት ጥቅምት 28/2007 ዓ/ም የከተማዋ ማህበረሰብ ስልጣን ላይ ያለው ስርአት እያራመደው የሚገኝ ኢ-ዴሞክራሲያዊ የአስተዳደር ዘይቤ በመቃወም፤ ያለምንም የሃይማኖት ልዩነት  መነሳት አለበት የሚል የወረቀት ፅሁፍ፤ በአደባባዮችና ትላልቅ ህንፃዎች ተለጥፎ መገኘቱን የተገኘው መረጃ ገለፀ፣
    መረጃው ጨምሮ የኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት ከአሁን በኋላ በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚነሳ ተቃውሞ እንደማይኖርና እንደተዳከመ እየገለፁ ባሉበት ሰአት በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ አከባቢዎች ተሰራጭቶ በተገኘው የቅስቀሳ ፅሁፍ የያዘው ወረቀት እጅግ እንደ አስደነገጣቸውና፤ በዚህ የተነሳም በከተማው ውስጥ በርካታ የፌደራል ፖሊስና ወታደሮች በመሰማራታቸው ምክንያት ህዝቡ እለታዊ ስራውን እንዳይሰራ ጫና ፈጥረውበት እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣