Friday, November 7, 2014

በትግራይ ክልል ታህታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች ለአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ሰብስበው አገራችን እድገት እሳያች ነው፤ የስራ እድል ተፈጥሯል እያሉ ቅስቀሳ ቢያደርጉም በህዝቡ ግን ተቀባይነት እንዳላገኙ ተገለፀ፣




     በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የታህታይ አድያቦ የእርሻ ልማት ሃላፊ ብርሃነ በርሄ የተባለው ካድሬ፤ ጥቅምት 18/2007 ዓ/ም ህዝቡን በመሰብሰብ ልማታዊ በሆነው መንግስታችን ምክንያት ገቢያችን በእጥፍ ጨመረ፤ አካባቢያችን ተለወጠ፤ ሰፊ የስራ እድል ተፈጠረ የሚሉና ሌሎች መንግስትን የሚያሞጉሱ ቃላቶችን ለማቅረብ በሞከረበት ሰአት፤ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበረው ህዝብ ግን ሃሳቡን እንዳልተቀበለው ለመረዳት ተችሏል፣
     ከህዝቡ የቀረበውን የተቃውሞ ሃሳብ ለመጥቀስ ያህል “እናንተ የስራ እድል ፈጥረናል እያላችሁን ነው፤ ወጣቱ ግን በስራ አጥነት ምክንያት ባህር አቋርጦ እየጠፋ ነው፤ በራሱ ጥረት በተለያየ የንግድ ስራ ለተሰማራም ከመደገፍ ይልቅ ከአቅሙ በላይ የሆነ ግብር በማስከፈል ወደ ድህነት አረንቋ እንዲገባ እያረጋችሁት ነው፤ እኛ የማናውቃት አገር አለችን እንዴ? ያለፈው ተግባራችሁ ይበቃናል ከእንግዲህ ወዲህ እኛን ማታለል እትችሉም።” በማለት መድረኩን ይመሩ ለነበሩት አመራሮች መቃወማቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣
    በመድሩኩ ክፉኛ ከተቃወሙት ወገኖች መካከልም ሃለቃ ካሕሳይ በርሀ የተባለው የዝባን ገደና ቀበሌ ስራ አስፈጻሚ የሚገኝበት ሲሆን፤  በካድሬዎቹ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰበትም ለማወቅ ተችሏል፣