Saturday, November 29, 2014

በአዲስ አበባ የሚኖሩ ወጣቶች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ እየተባሉ የስራ እድል እየተከለከሉ እንደሆነ ታወቀ።



  የ2007 ዓ.ም ምርጫ የሚካሄድበት ዕለት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር የተቃዋሚ ድርጅቶች ከሚያደርጉት ቅስቀሳ ጋር በተየያዘ የህዝብ ድጋፍ እንዳያገኙ ገዥው መንግስት የተለያዩ ተንኮሎች እየፈፀመ ሲሆን ነዋሪው ህዝብ ደግሞ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶችን ተቃዋሚ ሲደግፉ የታዘቡ የስርዓቱ ካድሬዎች ሰርተው እንዳይበሉ  እንደከልከሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳሪዎች ሃገር ተረካቢ የሆነውን ትውልድ ባለፉት ወራት ባካሄዱት ተደጋጋሚ ቅስቀሳ  የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  አባል መሆንን ነቅፎው እንደ አማራጭ የተቃዋሚ ድርጅትን በመደግፋቸው ምክንያት ትልቅ ስጋት ላይ የወደቁት የስርዓቱ አመራሮች ማንኛውም የስራ እድል ስለ ከለከሉት ነዋሪው ህዝብ በከፍተኛ የማህበራዊ ችግር ላይ እንዲወድቅ ማድረጋቸውና  ለዚህም ፍትህ ለማግኘት ብለው ወደ ድሪባ ኩማ አቤቱታ አቅርበው እስካሁን መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።