እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት ታህሳስ
16 / 2007 ዓ/ም ሌሊት በአማራና በትግራይ ክልል ነዋሪዎች መካከል ቀደም ብሎ ሲያጣላቸው በቆየው የመሬት ጉዳይ የተቀሰቀሰው
ግጭት የሁለቱም ክልል የሚሊሻ አባላት በከፈቱት ተኩስ በርካታ ህዝብ እንደሞተና የአካል ጉዳት እንደደረሰ የገለፀው መረጃው የተከፈተውን
ተኩስ ለማስቆም የተላኩ የፌድራል ፖሊሶችም ምንም ስራ መስራት እንዳልቻሉ ታውቋል።
መረጃው ጨምሮ ሁለቱንም ክልሎች እያጣላቸው ያለው መሬት ብዙ ጊዜ ያስቆጠረ እንደሆነ ከገለፀ በኋላ ስርዓቱም ሁኔታውን እልባት ሊያስቀምጥለት
ያልቻለው የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት መሳሪያ በመሆኑ ራሱ የሚፈጥረው የማጋጨት ተግባር መሆኑን በርካታ ታዛቢዎች ገልፀዋል።
በተመሳሳይ ይህ እንደመፍትሄ ተብሎ በሁለቱ ክልል ከፍተኛ ካድሬዎች አቶ ኪሮስ
ቢተው የግብርናና ገጠር ልማት ሃላፊ፥ ዘአማንኤል(ወዲ ሻንበል)የፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊ ሓድሽ ዘነበ የፀጥታ ሃላፊ ከትግራይ ክልል
ሲሆኑ ከአማራ ክልል ደግሞ የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊው፤ ይሳቅ አያሌው የፀጥታ ሃላፊ፤ መሃመድ ከድር የፖሊስ ኮሚሽን ተወካይና በሌሎች
ካድሬዎች በቀረበው ውሳኔ ያልተደሰተው የሁለቱም ክልሎች ህዝብ እናንተስ ልታስታርቁን ሳይሆን እርስ በርሳችን ልታገዳድሉን ነው የመጣችሁት
እየተገዳደልን እንኖራለን እንጂ ውሳኔያችሁን አንቀበለውም ማለታቸውን ተከትሎ ካድሬዎችም ውሳኒያችንን ካልተቀበላችሁ ይህ መሬት ካሁን
በኋላ ከሁለቱ ክልል ውጭ ሆኖ በፌድራል እንዲተዳደር ተወስኗል በማለታቸው ህዝቡም ውሳኔውን እንዳልተቀበለው ባለፈው የዜና እወጃችን
መግለጻችን ይታወሳል።
ከታህሳስ 4
እስከ 5/ 2007 ዓ/ም ወደ ሚያነታርከው ቦታ የሄዱ ቢሆንም ግን ምንም መፍትሄ ሳያስቀምጡ መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።