Sunday, January 25, 2015

በመቐለ ዩኒቨርስቲ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ በዩኒቨርስቲው ሃላፊዎች እንደተጠፋፋ ለማወቅ ተችሏል።



በመቐለ ከተማ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት ታህሳስ 23 /2007 ዓ/ም የአለፉትን የ10 ዓመታት የበጀት አጠቃቀም ኦዲት በተደረገበት ሰዓት 36 ሚሊዮን ብር በሃላፊዎች የተጠፋፋ መሆኑን ከስፋራው አስረድተዋል።
ቀደም ሲል እኒህ የዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች በላይነሽ ተስፋይ በሰራችው የሃሰት ሰነድ ሲያወራርዱ የቆዩ ሲሆን አሁን ግን በህጋዊ የመንግስት ሰነድ ሲወራረድ 36 ሚሊዮን ብር በመጥፋቱ በላይነሽ ተስፋይ የተባለችውን ደግሞ የሃሰት ማወራረጃ ሰነድ ሰርተሽ ገንዘብ እንዲጠፋፋ ምክንያት ሆነሻል በማለት የታሰረች ሲሆን ገንዘቡን የበሉት ሃላፊዎች ግን ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳልተጠየቁ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
  በመጨረሻም መረጃው እንደዚህ ዓይነት የሙስና ተግባር በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሳይሆን  ቀደም ሲል በአክሱምና በአዲግራት ዩኒቨርስቲዎችም የታየ መሆኑንና ተማሪዎችም በከባድ የማህበራዊ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች የገልፁ መሆናቸው ይታወሳል።