Sunday, January 25, 2015

ባለፈው ሳምንት የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓትን በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴ.ን/ መቀላቀላቸውን ከትህዴን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



ወደ ድርጅታችን ከተቀላቀሉት ወጣቶች የተወሰኑትን ለመጥቀስ-
-         መ/ር ጌታቸው ገ/ዝጊአብሄር ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን፤ ክልተ አውላዕሎ ወረዳ፤ ፅጌረዳ ቀበሌ ዲነዋለ ከተባለው አካባቢ፤
-         ካህሳይ ገ/እዚጊአብሄር። ከትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ሰቲት ሁመራ ወረዳ፤ 02 ቀበሌ
-         ወልዳይ ነጋሽ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ  ዞን፤ ታሕታይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ፀፀር ቀበሌ፤
-         ተሾመ ገ/ማርያም፤ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ  ዞን፤ ታህታይ አድያቦ ወረዳ፤ ለሰ ቀበሌ። ማይ ወይኒ አካባቢ፤
-         ዓንዶም አረጋይ ፤ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ሸራሮ ከተማ፤ ማይ ሙሴ ቀበሌ፤ ሃየሎም ከተባለው አካባቢ፤
-         በለጠ ስልጣን ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ጣንቋ አበርገለ ወረዳ፤ ለምለም ቀበሌ፤ በሊሕ ከተባለው ቦታ፤
-         ጣሂር ሑሴን ፤ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ፤ሽረ እንዳስላሴ ከተማ፤ ቀበሌ 03 ፤
-         ፃዕዳይ ኪዳነ፤ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ታህታይ አድያቦ ወረዳ፤ ዝባን ገደና ቀበሌ፤ ከላውሎ ከተባለው አካባቢ፤
-         ተኽሊት ገ/ፃዲቕ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ስሑል ቀበሌ፤ ደጀን አካባቢ፤
-         ፅጋቡ ደጀን ከትግራይ ደቡባዊ ዞን፤ ሕንጣሎ ወጅራት ወረዳ፤ ዓፈዓ ሰገድ ቀበሌ፤ ሓዋፁ ከተባለው አካባቢ፤
-         ገብረስላሴ አዲሱ ፤ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ደጉዓ ተምቤን ወረዳ፤ መገስታ ቀበሌ፤ ሩባ ካሳ ከተባለው አካባቢ፤
-         ወታደር ፍፁም ሙሉነህ ፤ከደቡብ ክልል፤ ወላይታ ዞን፤ ህንቦ ወረዳ፤ 01 ቀበሌ የሆነና፤ በ 8 እዝ ሜካናይዝድ ፤የሻለቃ ሃኪም ሆኖ ሲያገለግል የቆየ፤
-         ፍፁም ገብረሂወት እና ሞገስ ጉዑሽ ሁለቱም ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ታሕታይ አድያቦ ወረዳ፤ ገማሀሎ ቀበሌ፤ ሰንበል አካባቢ፤
-         ነጋሲ ሃድጉ ፤ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ ታሕታይ ማይጨው ወረዳ፤ ምሬና ቀበሌና ሌሎችም የሚገኙባቸው ሲሆኑ ወደ ትግል ለመሄድ ያነሳሳቸውን ምክንያት ሲገልፁ ህዝቡ በማህበራዊ አገልግሎት እጥረት ተማርሮ ጥያቄዎችን ስላስነሳ ብቻ በተቃዋሚ ደጋፊነት ተፈርጆ በስርዓቱ በደል እየደረሰበት በመሆኑና በሌሎችም ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል።
   በተለይ ፅጋቡ ታደሰ የተባለው ወጣት በማረት ሆኖ እየሰራ በነበረበት ግዜ መዋጮ እንዲከፍል እያስገድዱት እንደነበሩና ከመጠን ያለፈ አድልዎ እንደሚካሄድ፤ ሁኔታውን አስመልክቶ ሂስ በሚያደርግበት ሰዓትም በላዩ ላይ የማስፈራራት ዛቻ ይደርስበት እንደነበር የገለፀ ሲሆን፤ መምህር ጌታቸው ገብረዝጊአብሄር በበኩሉም አንድ መምህር 6 አይነት ትምህርት እንድያስተምር ስለሚገደድና ከመጀመርያውም የአንድ አስተማሪ የስራ መመዘኛው በድርጅቱ አባልነት ታይቶ ወደ ስራው ስለሚቀጠር በትምህርት ጥራት ላይ እንቅፋት እያደረሰ በመሆኑ እንዲታገል እንደወሰነ ተናግሯል።