አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ለይስሙላ ምርጫ ለማካሄድ ላይና ታች እያለ
ባለበት ሰዓት በጎንደር ከተማ በሚገኘው የምረጫ ጣቢያ የነበሩ ንብረቶች ማለት እንደጠረጴዛ፤ ወንበርና ሌሎችም ለምርጫ የሚያገለግሉ
ቁሳቁሶች ጥር 24/2007 ዓ/ም ጠፍተው እንዳደሩ ሊታወቅ ተችሏል።
ህብረተሰቡ በስርዓቱ አስመሳይ ‘ምርጫ ላይ እየወሰደው ያለው እርምጃ እየተባባሰ
በመሄድ ላይ በመሆኑ አሁን በጎንደር ከተማ የተደረገውም የመጀመርያ እንዳልሆነ የገለፀው መረጃው በተጨማሪም የሰሜን ጎንደር ከተማ
ነዋሪ ህዝብ ማህበራዊ ችግሮቻችን ካልተፈቱ የምርጫ ‘ካርድ አንወስድም በማለት የተቃውሞ ድምፅ በማሰማት ላይ እንደሚገኝ ከዚህ በፊት
በዜና እወጃችን ላይ መግለፃችን ይታወሳል።