Friday, February 27, 2015

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የሚገኙ መምህራን በሰማእታት ታጋዮች ቤተሰቦቻቸው ሰም ገንዘብ እንዲያዋጡ በስርአቱ የተሰጣቸው ትእዛዝ ቅንነት የጎደለው ነው ሲሉ እንደተቃወሙት ያገኘነው መረጃ አመለከተ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን አስገደ ፅምብላና ታሕታይ ቆራሮ የሚገኙ መምህራንና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች በሰማእታት ታጋዮች ቤተሰቦቻቸውና ልጆቻቸው ስም በመሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ከገለፀ በኋላ  ተሰብሳቢዎች ግን መንግስት እስከ አሁን ድረስ የት ቆይቶ ነው፤ አሁን ምርጫ ሲባል ነው ወይ የሰማእታት ቤተሰቦች አዛኝ መስሎ በመቅረብ ህዝብ ለማደናገር እየተጠቀምበት ያለው መላ ነው በማለት እንደተቃወሙት ታወቀ።
ተሰብሳቢዎቹ በማስከተል “ የሰማእታት ቤተሰቦችና ልጆቻቸው በመንግስት ለምን አይታገዙም፤ የሰማእታት ስም እያነሳህ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም፤ በሰማእታት ስም ከህዝብ የሚዋጣው ገንዘብ ለካድሬዎች ኪስ መሙያና ለድርጅቱ ኩባንያዎች  ማጠናከሪያ እንዲውል እንጂ ለሰማእታት ቤተሰቦች የሚሰጣቸው አካል የለም” በማለት ትእዛዙን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።