Friday, February 27, 2015

የቃፍታ ሁመራ ወረዳ ህዝብ ስልጣን ወደ አዲሱ ትውልድ መተላለፍ መቻል አለበት በማለት ሊካሄድ የታሰበውን ምርጫ እንደተቃወመው ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የቃፍታ ሁመራ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ ወገኖቻችን በወረዳው አስተዳዳሪ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ/ም በተካሄደ ስብሰባ አዜብ መስፍንን ትመርጣላችሁ አትመርጡም? የሚል አጀንዳ እንደነበር የገለፀው መረጃው ተሰብሳቢው ህዝብ በበኩሉ ለ24 አመታት መርጧት እየተባልን ለሰለቸችን ኣዜብ ይቅርና የእኛ ፍላጎት ስርዓቱ እንዲቀየር ነው በማለት እንደተናገሩ ታውቋል።
 ነዋሪዎች ጨምረውም የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ስልጣኑን ወደ አዲሱ ትውልድ እናሸጋግረዋለን ካላችሁን ስንት አመታት ተቆጥሯል በተግባር ግን  እኛን ብቻ ምረጡን እያላችሁ ለውጥ የሚባል ነገር ስለሌላችሁ ህዝብ በይስሙላ ምርጫችሁ ተስፋ ቆርጧል ሲሉ ከገለፁ በርካታ ዜጎች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ሃለቃ ይስማው ፋንታው አቶ ሹመንዲ አቶ ገብረስላሴና ሌሎችም እንደሆኑ ምንጮቻችን ከስፍራው ገልፀዋል።