ምንጮቻችን እንደገለፁት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ
ወረዳ ምድረ-ፈላሲ ቀበሌ የሚገኙ ምልሻዎች በአካባቢው ቅኝት ለማድረግ በሃላፊዎቻቸው ታዝዘው ወደ በረሃ በሄዱበት ጊዜ ገብረሂወት
ካሕሳይ የተባለው ምልሻ ለቅኝት ከወጡት ምልሻዎች ጋር ጥር 28
2007ዓ/ም ሌሊት ላይ ቦታ በያዙበት ሰአት ወደ መኝታው ቦምብ በመጣል እግሩን እንዲቆረጥ ማድረጋቸው ታውቋል።
እነዚህ
ምልሻዎች በአካባቢው አስተዳዳሪዎች ታዝዘው እንጂ ለዚህ ተግባር አምነውለት እንዳልፈፀሙት ከገለፀ በኋላ የአደጋው ምክንያት ምንድነው? ተብለው በሃላፊዎቻቸው በተጠየቁበት ጊዜ ጠላት አጋጥሞብን ነበር
በማለት ሃቁን ሊሸፋፍኑት እንደሞከሩና ይሁን እንጂ ጉዳቱን የደረሰበት ምልሻ ግን ሆን ብለው ራሳቸው ናቸው የጣሉብኝ ጠላት የሚባል
አላጋጠመንም በህግ ይጣራልኝ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።