Friday, February 27, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ-ዳሞት ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤት ሰራተኞች በመንግስት ጭቆና ተማርረው ከስራቸው እየለቀቁ መሆናቸውን ከስፍራው የደርሰን መረጃ አመለከተ።



   እንደመረጃው ገለፃ በደጋ-ዳሞት ወረዳ ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሰሩ የቆዩ ሰራተኞች እስካሁን ከመንግስት ማግኘት የሚገባቸውን የትምህርት ዕድል  የደመወዝ እድገትና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ካለማግኘታቸው ባሻገር መጪውን የ2007  ምርጫ አስመልክቶ ከወዲሁ በጥርጣሬ አይን እየታዩ ጫና ስለበዛባቸው በገዛ ፈቃዳቸው ከስራ ገበታቸው እየለቀቁ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
   ምንጮቻችን እንደገለፁት የመንግስት ከፍተኛ ግፍና ጫና ካስመረራቸው የወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች መካከል እንደአብነት በወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት  ፅህፈት ሃላፊ በሆነው በዝይን እውነቱ ጫና ደርሶባቸው በቅርቡ ብቻ ከ32 በላይ የሚሆኑ የሚሆኑ የግብርና ባለሙያዎች ከስራ ገበታቸው የለቀቁ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህልም አቶ አንሙት ስንሻው፥አቶ ነፃነት አዱኛ፥ አቶ አንዱዓለም አድነው፥አቶ ምናለ መኮነን፥ አቶ መላክ ታደገ፥አቶ ይግዛው አበበ፥ አቶ ዳኘ ታደሰ፥ አቶ ብርሃኑ አለህኝ፥ ወ/ሮ ጥሩ መኮነን፥አቶ ይበልጣን፥ወ/ሮ ብርሃን ሽፈራው ፥አቶ በላይ መኮነን፥ አቶ ከፋለ  ስንሻው፥አቶ ልጃለም እሱባለው፥ አቶ ይከበር ደሴ፥ አቶ ግርማ ባይሌ፥አቶ ገበያው አረጋ፥ ጥሩዓለም መግባሩና ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ በመንግስት ጫና ምክንያት ስራቸውን መልቀቃቸው ታውቋል።