በሑመራ
ከተማ አውቶቡስ ተራ አካባቢ በሸቀጣ ሸቀጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩት ወገኖች ባለፈው ክረምት ቤታቸው እንዲፈርስ ከተደረገ
በኋላ በሱ ፋንታ በህጋዊ መንገድ በካሕሳይ አበራ ሆስፒታል አካባቢ መሬት ተሰጥቷቸው በንግድ ስራ ላይ ሲሰሩ ቆይተው እንደገና በአዲስ
መልክ በከተማዋ አስተዳዳሪዎች ከጥር 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በህጋዊ መንገድ የተሰጣቸውን መሬት ህጋዊ አይደለም በማለት ድርጅታቸው
እንደታሸገ ተገለጸ።
ነጋዴዎች
በበኩላቸው የከተማዋን አስተዳዳሪዎች አንዱ ሰጪ አንዱ ቀሚ ሆነው እየሰራንበት የነበርነውን ድርጅታችንን በማፍረስና በመዝጋት ለኪሳራ
መዳረጋችን ሳይበቃ እንደ ዜጋ ሳንታይ ህጋዊ መሬታችንን ተከለከልን በማለት ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።