Wednesday, March 25, 2015

በሽረ እንዳስላሴ የሚገኘው እስር ቤት በእስረኞች ተጨናንቆ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከስፍራው የላኩልን መረጃ አመለከተ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽረ ከተማ የሚገኘው እስር ቤት ከመጠን በላይ በእስረኞች ተጨናንቆ ስለሚገኝና ለበርካታ አመታት የታሰሩ የአካባቢው ተወላጆች የካቲት 23/ 2007 ዓ/ም ወደ አክሱም፤ አዲግራትና መቐለ እንደወሰዷቸው ታውቋል፣
 ወደሌላ እስር ቤት ከተወሰዱት እስረኞች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ጌታቸው ገብረ አናንያ እና ለሞት የተፈረደው ጥላሁን ባራኺ የተባሉትና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው የገለፀው መረጃው እስረኞች በበኩላቸው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ታስረን እያለን አሁን ደግሞ ቤተሰቦቻችን በአቅራቢያቸው እንዳያዩን እያራቁን ናቸው በማለት ምሬታቸውን እየገለፁ እደሚገኙ አስረድቷል፣