Wednesday, March 25, 2015

በአብርሃ ጂራና አካባቢው የሚኖር ህዝባችን ፀጉረ ልውጥ እየተባለ በአካባቢው የፀጥታ አካላት እየተሰረ እየተንገላታ መሆኑ ታወቀ፣



 በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል አብርሃ ጂራ  አካባቢ የሚኖር ህዝብ በስርዓቱ የፀጥታ አካላት እየታሰረ እየተንገላታ መሆኑን የገለፀው መረጃው በቅርቡ ብቻ  እንኳን ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ አራት ወጣቶች ፀጉረ ልውጥ ተብለው በአብርሃ ጂራ እስር ቤት ለ2 ሳምንታት ያህል ታስረው ሲሰቃዩ እንደቆዩ አስረድቷል፣
እነዚህ ምንም በደል ያልፈፀሙ ወጣቶች ከሁለት ሳምንት እስር በኋላ ዞሮ የሚያያቸው የመንግስት አካል ባለማግኘታቸው የእስር ቤቱን ቆርቆሮ ቀድደው እንዳመለጡና የእስር ቤቱ የጥበቃ ተረኛ መኮነን የነበረ ዋና ሳጂን ሳላቸው ግርማ የተባለውን  ሆነ ብለህ ጉቦ ተቀብለህ ለቀሃቸዋል ተብሎ ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣