Tuesday, March 3, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን መጪውን ምርጫ አስመልክቶ መንግስት የተለያዩ ንፁሃን ዜጎችን በማሰር ተግባር ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ በየአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።



   በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ-ሰላም፤ ጂጋ፤ ደምበጫ፤ ቡሬና ማንኩሳ ከተባሉ ከተሞች ከየካቲት 1 ቀን 2007ዓ/ም ጀምሮ ከ14 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአምባገነኑ መንግስት ተላላኪ ፌድራል ፖሊሶች እየተለቀሙ አድራሻቸው የጠፋ መሆናቸውና በተለይ ጂጋ ከተማ ውስጥ በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረው አቶ አንዷለም የተባለው የቀድሞ የደርግ ወታደር አባል የትጥቅ ትግል ለሚያካሂዱ ተቃዋሚዎች ከፍተኛ እገዛ አድርጓል በሚል ሰንካላ ምክንያት በስውር  ሳይገደል እንዳልቀረ መረጃው አስረድቷል።
    በተጨማሪም ከጃቢጠህናን ወረዳ ወርቅማ ከተባለው አካባቢ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ስራ ይጠባበቁ የነበሩ ሁለት የዲግሪ ተመራቂዎች ባልታወቀ ምክንያት በፌድራል ፖሊስ ከተያዙ በኋላ እስካሁን አድራሻቸው እንዳልታወቀ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።