Tuesday, March 3, 2015

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ከማሽ ዞን፤ መጪውን ምርጫ ለማስከበር በሚል በመንግስት የተሰማሩ የክልሉ ልዩ ሃይሎች በነዋሪው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀሙ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



    በገዥው መንግስት የተሰማሩ ተላላኪ የክልሉ ልዩ ሃይሎች በነዋሪው ማህበረሰብ ላይ አረመኔያዊ ግፍ እየፈፀሙ መሆናቸውና በከማሽ ዞን በሎጂ-ጋንፎ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ተንቀሳቅሰው ዕለታዊ ስራዎቻቸውን መስራት እንዳልቻሉ የገለፀው መረጃው እንደአብነትም በሎጆ-ጋንፎ ወረዳ የምርጥ ዘር ድርጅት አምራች የሆኑ ኢንቨስተሮችንና ነጋዴዎችን የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ/ም የክልሉ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በመያዝ ያለምንም ምክንያት አስረው ማሳደራቸውንና በኋላም ጉቦ እንዲከፍሉ በማስገደድ ሊፈቷቸው እንደቻሉ ሊታወቅ ተችሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓ/ም 3 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሆኑ ወጣቶችን አሸባሪዎች በሚል ምክንያት አሶሳ እስር ቤት በመወሰድ እያሰቃዩዋቸው መሆኑን ከስፍራው የደርሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።