Tuesday, March 31, 2015

በአዊ ዞን የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ለቅስቀሳ የተከራዩትን አዳራሽ መከልከላቸው ከስፍራ የሚገኙ ምንጮቻችን ገልጹ፣



በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች   የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምህፃሩ አገዴፓን ጨምሮ የሰማያዊና የመኢአድ አባላት ለቅስቀሳ በዚገም ወረዳ የወረዳውን የህዝብ አዳራሽ ና በኮሶበር ከተማ ቀበሌ 2 የተከራዩት የህዝብ አዳራሽ የተከለከሉ ሲሆን በተመሳሳይ በዳንግላና በጓንጓ ወረዳዎችም የተከለከሉ መሆኑን ምንጮቻችን ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣
 ይህን የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ከስሩ ለማጥፋት ውስጥ ለውስጥ የተሰማሩት የደህንነት አባላት አንዳንዶቹ ተልኮአቸውን ሲገልፁ እንደተደመጡት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠን ትዕዛዝ በመሆኑ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰብሰቢያ አዳራሽ የመፍቀድ መብት የላቸውም በማለት የዚገም ወረዳ አስተዳዳሪ ለአገዴፓ የፈቀደውን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የወረዳው የባህልና ቱሪዝም ሃላፊ ሰለሙን ስንታየሁ የተባለ እንደከለከላቸው  የደረሰን መረጃ አስረድቷል፣