Tuesday, March 31, 2015

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሶጌ ወረዳ ከክልሉ ፈቃድ ውጭ የራሳቸውን ሰንደቅ አላማ እየሰቀሉ የሚገኙ የጉሙዝ ብሄሮች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ፣



እንደ ምንጮቻችን ገለፃ  በክልሉ ሶጌ ወረዳ የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው  የጉሙዝና ጥቂት የበርታ ብሄሮች ባለፉት ሁለት ወራት ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን በሚል የተቃዋሚ ሰንደቅ አላማ  መስቀላቸውን ተከትሎ በቅርቡ መንጌ በተባለው  ወረዳ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ቀስቃሽ ናችሁ በማለት በገዥው መንግስት ተላላኪ ፖሊሶች  የሁለቱ ብሄር ዜጎችን ነጥሎ በማውጣት ከፍተኛ ድብደባ  እየደረሰባቸው መሆኑን አስረድተዋል፣