Tuesday, March 31, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮች ከመኖሪያ አካባቢያቸው እየተባረሩና በምክንያት እየታሰሩ መሆናቸውን ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



በመረጃው መሰረት በዞኑ የሚንቀሳቀሱ የመደረክና ኢራፓ እንዲሁም  የአንዳንድ ተቃዋሚ አባላት ከመኖርያ አካባቢያቸው እየተባረሩ ሲሆን እንደአብነትም በቡሬ ወረዳ መድረክን ወክለው ይንቀሳቀሱ የነበሩ አቶ አበራ ታየና አቶ ዋለልኝ አስማረ የተባሉ በከተማው ቀበሌ 04 አቦ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከራዩትን ቢሮና የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ለቀው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን በቡሬ ወረዳ ደረቋ በተባለው አካባቢ ይኖር የነበረ ወታደር አዝመራው ከፋለ ደግሞ ታፍኖ ከቆየ  ከሳምንታት በኋላ አዲስ አበባ  ማዕከላዊ እስር ቤት በአሰቃቂ ሁኔታ እየተሰቃየ መሆኑን ታውቋል፣   
  በተመሳሳይ በጃዊ ወረዳ የትራፊክ ፖሊስ ዋና ሳጂን የሆነውን አበጀን ጨምሮ  24 ዜጎች የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው ከየ ጽሕፈት ቤት ሃላፊዎቻቸው ጋር ባለመስማማታቸው ብቻ ከግንቦት 7 እና ከትህዴን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ዳብዛቸው የጠፉ። አቶ መኮነን አብየ። በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረ  አቶ ፈንታ። አቶ ጥላሁንና ሌሎች የሚገኙባቸው መታሰራቸውን ባለፈው የዜና እወጃችን መዘገባችን ይታወቃል፣