Tuesday, March 31, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ የመንግስት ሰራተኞች ከመስሪያ ቤታቸው ሊታገዱ እንደሚችሉ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው መሆናቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣



እንደምንጮቻችን ገለፃ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የምርጫ ካርድ ያለወሰዱ የመንግስት ሰራተኞችን የመለየት ሥራ ሲሰራ መሰንበቱን የገለፀው መረጃው በተለይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በከተማ ልማት ጽሕፈት ቤትና በጤና ተቋማት ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሚገኙ የምርጫ ካርድ ባልወሰዱ ባለሙያዎችና ሰራተኞች  ላይ የወረዳው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሳሙኤል የተባለ በግልፅ ከፍተኛ ዛቻ ሲዝትባቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፣
የምርጫ  ካርድ ያልወሰዱ የወረዳ 8 የጤና ተቋማትና የከተማ ልማት ጽሕፈት ቤት ሰራተኞችና ባለሙያዎች በበኩላቸው ለ5ኛ ጊዜ የሚካሄደው ምርጫ ትርጉም የለውም በማለት እንደማይሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፣