Thursday, March 26, 2015

በጎንደር ከተማ የብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ብዱን የማይተገበር ቃል እየገባ የሚያደርግውን የምረጡን ቅስቀሳ ነዋሪው ህዝብ እየተቃወመው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣



በአማራ ክልል የሚኖር ህዝብ በብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች ላይ የነበረው እምነት በአሁኑ ጊዜ የወደቀ መሆኑን የገለፀው መረጃው ይህን የወደቀ እምነት ለመመለስም በጎንደር ከተማ ዙሪያ ሲታዩ የቆዩትን ስህተቶቻችን አስተካክለን በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኘው ህዝባችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመዘርጋት እናስተካክለዋለን በማለት አዳዲስ ቃል ቢገቡም። ነዋሪው ህዝብ ግን ዳግም አንታለልም በማለት እንደተቃወማቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    በጎንደር ህዝብ እየቀረቡ ካሉ የተቃውሞ ሃሳቦች መካከል መጀመሪያ የዜጎች ሰብዓዊ ዲሞክራሲያዊ  መብት ሳይሸራረፍ መከበር አለበት፤ የዜጎች መብት በአፈሙዝ አታፍኑ፤ ለራሳችሁና ለሸሪኮቻችሁ እንጠቀም የሚል ተግባር አቋርጡ፤ ሙስና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርኣት መገለጫ ነው፤ ተቃዋሚ ድርጅቶች ፕሮግራምና አላማቸውን ለህዝብ እንዳያስተዋውቁ በሌሊት ታፍናላችሁ ይህንና ሌላ ስር የሰደዱ ችግሮች ሳይቀረፉ በብዓዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስር ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አይካሄድም በማለት የደረሰን መረጃ አመልክቷል፣
    ይህ በብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ጉጅሌ አመራሮች በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የሰነበተ ቅስቀሳ ከመጋቢት 4 /2007 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ተለያዩ የገጠር ከተሞች እየተስፋፋ እየቀጠለ ሲሆን ህዝብ ግን እንዳልተቀበለው ለማወቅ ተችሏል፣