Thursday, March 26, 2015

በምዕራብ ትግራይ ዞን የሚገኙ የፖሊስ አዛዦችን የትግራይ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ሃዱሽ ዘነበ ማስፈራሪያ የተሞላበት ስብሰባ ላይ ጠምዷቸው እንደዘነበት ታወቀ፣



በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ የፖሊስ አዛዦችንና መርማሪዎችን በክልሉ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ሃዱሽ ዘነበ ከመጋቢት 9 እስከ 10 2007 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ ራሱ በህዝብ ላይ ግፍ እየፈፀመ እንዳልነበረ ንፁህ መስሎ በመቅረብ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ህዝብ ድርጅታችን ህወሃትን በጥላቻ እያማረረ ስለሆነ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ከከሰርን በእናንተ ምክንያት መሆኑን እወቁ እያለ እንዳስፈራራቸው ተገለጸ፣
   በዚህ ለሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የተገኙ የፖሊስ አባላት አንዳንዶቹ በታቀደው ሴራ ፈርተው መጥፎ ስራ አልሰራንም በማለት ራሳቸውን ሲከላከሉ ሴራውን ቀድመው የተረዱት ደግሞ የአሰራሩ ደጋፊዎች በመምሰል ችግሮቻችንን በየቀኑ ህዝባችን እየገለጸልን ነው ሲሉ። ራስ በራሳቸው እንዲገማገሙ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
    ይህ በአዛዦችና በመርማሪ ፖሊሶች መካከል የተካሄደ ስብሰባ በትግራይ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እየቀጠለ መሆኑን የገለፀው መረጃው። ህዝብን በማታለል ለሚካሄደው ምርጫ ለማሸነፍ የተደረገ የህዝብ ጠበቃ መስሎ ለመቆም ያለመ መሆኑን  አስረድቷል፣