Sunday, March 29, 2015

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህዝብ አመፅ እንዲያነሳ እየቀስቅሳችሁ ነው ተብለው በኢህአዴግ ፌደራል ፖሊሶች ታፍነው እየታሰሩ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ገለፀ፣



ባገኘነው መረጃ መሰረት። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ምርጫችን ለማደናቀፍ ህዝብ አመፅ እንዲያነሳሳ ስትቀሰቅሱ ቆይታችኋል በሚል ምክንያት። በኢህአዴግ አፋኝ የፌደራል ፖሊስ ታፍነው እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። ከታሰሩት መካከልም ሁለት የሁለተኛ አመት የህግ ተማሪዎችና ሌሎች ሶስቱ ደግሞ የጆኦግራፊ ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፣
    እነዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወገኖቻችን።  እስካሁን የት እንደታሰሩ አድራሻቸው እንዳልታወቀና። በዚህ ምክንያትም በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን በከፍተኛ ውጥረት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣