Sunday, March 29, 2015

በትግራይ ደቡባዊ ዞን የጨርጨርና የመሆኒ ነዋሪዎች በዞኑ ወገናዊነትና ጉቦ ሰፍኖ ፍትህ የሚባል ነገር የለም ሲሉ። በዞኑ አመራሮች ላይ ብሶታቸው እንዳቀረቡ ተገለፀ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በትግራይ ደቡባዊ ዞን ጨርጨርና መሆኒ የሚገኝ ህዝብ የካቲት 22/ 2007 ዓ/ም በተካሄደ ስብሰባ ላይ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ ጉቦና ወገናዊነት ስለ ነገሰ። ለምርጫ አንመዘገብም በማለት መቃወማቸው ታውቋል፣
   መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው። የዞኑ አስተዳዳሪ የሆነው አቶ ሃፍቱ ወላሞ ያለአግባብ ለቤተሰቦቹ መሬት እያደለ በመሆኑ። በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳጣ የገለፀው መረጃው። በዞኑ ከፍተኛ ክርክር ከተካሄደ በኋላ መልካም አስተዳደር የለም ፍትህ ያስፈልገናል በማለት። ጠንክረው በመቃወማቸው የትግራይ ክልል ምክትል አስተዳዳሪና የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ካድሬ ኪሮስ ቢተው። ወደ ቦታው በመሄድ ሊያወያያቸው ቢሞክርም። መረዳዳት ሳይችሉ እንደቀሩ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣