Sunday, March 29, 2015

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳ የሚገኙ የሚልሻ አባላት መሳሪያቸው እየተቀሙና እየተገደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው የላኩልን መረጃ አመለከተ፣



     በመረጃው መሰረት። በፀገዴ ወረዳ ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ ሒላብ በተባለው አካባቢ። ካሳ ረታ የተባለው ወገን ከ16 ጓደኞቹ ጋር በመሆን ህዝብ እያሰቃዩ የነበሩትን 12 ምልሻዎች። መሳሪያቸውን እንደቀሟቸውና ትጥቃችንን አንሰጥም ላሉት ለሚሊሻ አስራት አለባቸውና የፖሊስ አባል የሆነውን ዘውደ አሽብር የተባሉትን  በጥይት መትተው እንደገደሏቸው ለማወቅ ተችሏል፣
  ይህ በሚልሻዎችና ሌሎች ታጣቂዎች ላይ ትጥቃቸውን በማራገፍ የተካሄደው የመግደል እርምጃ። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ መልኩ መፈፀሙን ይታወቃል፣