Tuesday, March 31, 2015

በአዊ ዞን የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በገዥው መንግስት እየታሰሩ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



 ምንጮቻችን ከደረሰን መረጃ መሠረት በዞኑ በሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የደህንነት አባላትና የታጠቁ ሃይሎች  ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ነፃ ዜጎችን የሃሰት ጥላሸት በመቀባት እያፈኑ በማጥፋት  ለስቃይ ለእንግልትና ለሞት ምክንያት እሆኑ መሆኑን የገለፀው መረጃው ከጃዊ ወረዳ ቀዝቀዝ ከተባለው ቀበሌ ሁለት ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ ዜጎች ታፍነው መወሰዳቸው ለማወቅ ተችሏል፣
 በተጨማሪም በአንከሻ ወረዳ አቶ ዘርይሁን ባንቲሁን የተባለ የመኢአድ አባል በዚህ በመጋቢት ወር ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት አየሁ ጤና ጣቢያ ሲታከም ቆይቶ እንደወጣ መውጣቱን የሰሙ ተላላኪ የፖሊስ አባላት በድጋሜ የአቶ ዘርይሁን ህይወት ለማጥፋት  መጋቢት 19 ቀን 2007 ዓም  ሃብታሙ ካሳሁን በተባለው ሚሊሻ ጠቋሚነት 5 ፖሊሶች አየሁ እርሻ ልማት ቀበሌ  ገመዳ ስላሴ ጎጥ እየጠበቁት እንደነበር ምንጮቻችን አስረድተዋል፣
ከዚህ ቀበሌ ሳንወጣ ተላላኪ የፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎች በመሆን አቶ ዘርይሁን ባንቲሁንን ግማሽ ሄክታር በርበሬ “ቱፎር ዲ” የተባለ  ፀረ አረም የረጩበት ሲሆን ተከታዩና አባሎቹ የሆኑትን እነ ጌታቸው አስረሳ። አልጋነህ ተጫነ። ዘመኑ አስማረና አሰፋ ገዳሙ የተባሉ ወጣቶች እንደማንኛውም ወጣት የታደላቸውን መሬት ተነጥቀው የትውልድ አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣