Saturday, March 21, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ የሚገኙ መምህራን መጪውን ምርጫ አስመልክቶ የተደረገላቸውን ቅስቀሳ እንደተቃውሙ ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት አመለከተ፣



በደረሰን ሪፖርት መሰረት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ማለትም ቁጭ 01፤ ዛልማና አለፋ እንዲሁም ሰንቶም በተባሉ አካባቢዎች የውሃ፤ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና አጠቃላይ የመሰረት ልማት አውታሮች  አለመሟላታቸው በተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄዎች መሆናቸውን የተገነዘቡት የየትምህርት ቤቶች መምህራን። መጪውን ምርጫ በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ የቀረበላቸውን የምረጡኝ ቅስቀሳ በእጅጉ መቃወማቸው ታወቀ፣
    በተለይ መምህራኑ ካነሱት ጥያቄ ውስጥ ከደብረ ማርቆስ ቁጭ በአየሁ ወደ ሱዳን ያልፋል በሚል ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ከፍተኛ ገንዘብ የተበጀተለት መንገድ እንኳን አስፋልት ሊገነባ ጥርጊያው አልተጀመረም። ስለዚህ ይህ መንግስት ምርጫ ሲመጣ የሚያወራው እንጂ በተግባር የለም በማለት የተቃወሙበትን ሃሳብ መድረኩን ይመራ የነበረው የወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ተወካይ ከሃቅሜ በላይ ነው በእርግጥ ይህንን እቅድ አውቃለሁ እስካሁን አለመሰራቱ ግን ለእኔም እንቆቅልሽ ነው ሲል መልስ መስጠቱ የበለጠ ለመማህራኑ እንዳናደዳቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣