Friday, March 13, 2015

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ ቢያራ አካባቢ የሚገኙ የገዢው ኢህአደግ ቡድን የሰራዊት አዛዦች በመኪና እየጫኑ ጥይቶችን በመሸጥ ላይ እንዳሉ ተገለፀ።



በባድመ አካባቢ ልዩ ስሙ ቢያራ የሚገኙ የማእከላይ እዝ፤ የ22 ክፈለ ጦር የሰራዊቱ አዛዦች በስርአቱ ላይ ያላቸው እምነት እየቀነሰ በመሄድ ላይ ሰለሆነ ትጥቅና ጥይቶችን ከመጋዘን አስወጥተው በመኪና እየጫኑ በመሸጥ ላይ እንዳሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
   መረጃው በማከል በዚህ አስነዋሪ ስራ ላይ ተሰማርተው ካሉት ወታደራዊ አዛዦች መካከል ሻምበል አደም ከማል ሲሆን እሱ የካቲት 5 /2007 ዓ/ም በታርጋ ቁጥር 02612 ፓትሮል መኪና 13 ሺህ ጥይትና ሌላ ትጥቅ ጭኖ ለመሸጥ በመጓዝ ላይ እያለ በዓዲ ሃገራይና ዓዲ ዓውዓላ መካከል እንደደረሰ በፖሊስ አባላትና በመከላከያ ሰራዊት እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህን አይነት አስነዋሪ ተግባር የኢህአደግ ቡድን የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከላይኞቹ ሃላፊዎቻቸው ጋር በመመሻጠር የፈፀሙት መሆኑንና  በሻምበል አደም የተፈፀመው ወንጀልም የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች እጅ እንዳለበት የክፍለ ጦሩ አባላት መነጋገሪያ አጀንዳቸው አድርገውት እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድቷል።