Friday, March 13, 2015

በዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩ መምህራንና ተማሪዎች ለህልውናችን ፀር ተንቀሳቅሳችኋል በሚል የሃሰት ውንጀላ ገዥው የኢህአዴግ ስርዓት እየገደላቸው መሆኑን ተገለጸ።



   ባገኘነው መረጃ መስረት በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ገዥው ቡድን ፖሊቲካዊ ትግል የሚያካሄዱ ድርጅቶች በተለያየ ጊዜና ቦታ ከህዝባቸው ጋር በመገናኘት ሲያካሄዱት በቆዩት ቅስቀሳ ላይ በመሳተፋቸው ምክንያት ፀረ መንግስት እንቅስቃሴዎች ስታካሂዱ ቆይታችኋል በማለት የካቲት 8/2007 በርካታ የዩንቨርስቲ መምህራኖችንና ተማሪዎችን እንደገደሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
   በአምባገነኑ ስርዓት የሞት ሰለባ ከሆኑት ንፁሃን ዜጎቻችን መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ይኩኖ-አምላኽ ኢሳያስ፤ ጌታነህ አስማረ፤ ኢንጅነር አባተ( ቻርተር) የሚባሉት ሶስቱም በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሲያስተምሩ የነበሩ ሲሆኑ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ በምስራቅ እባኮ የጋምቤላ ብሄር ተወላጅ የሆነ የዩኒቨርስቲ ተማሪም የፈፀምኩት ወንጀል ሳይኖረኝ አልታሰርም ስላላቸው ብቻ የስርዓቱ ወሮ በላ ታጣቂ ካድሬዎች በዱላ ደብድበው እንደገደሉት ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል።