Thursday, March 26, 2015

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ዙሪያ ወረዳ፤ መንጌ በተባለው አካባቢ በርካታ ህዝብ የተገኘበት ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፣



  እንደምንጮቻችን መረጃ መሠረት ከሸርቆሌ ወደ አሶሳ ከተማ በሚወስደው መንገድ። መንጌ በተባለው ቀበሌ አካባቢ መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ/ም በርካታ የተቃዋሚ አባል የተገኘበት ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን። የተለያዩ ተሸከርካሪዎችም ከማለፍ ተቆጥበው ሰላማዊ ሰልፉን በማጀብ ድምቀት የሰጡት መሆኑን የተረዱ የገዥው መንግስት ተላላኪ የፖሊስና የመከላከያ አባላት። በአቅራቢያው ከአሶሳ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በአስቸኳይ በመምጣት ሰልፉን ለመበተን ቢሞክሩም። ህዝቡ ግን ከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ ለረጂም ሰዓት ሳይደናገጥ ተቃውሞውን እንደገለጸ ታውቋል፣
    ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳንወጣ። ባምባሲ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችን። የገዥው መንግስት ተላላኪ ካድሬዎች በመሰብሰብ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንዲመርጡ ያቀረቡትን ቅስቀሳ መቃወማቸውን ተከትሎ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ካልመረጡ በኢንቨስትመንትና በነዋሪነት  የተሰጣቸውን የእርሻ መሬት እንደሚቀሙ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣