Thursday, March 26, 2015

በሃገር አቀፍ ደረጃ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሎች የስፖርት ውድድር ለማሳተፍ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የመጣ አንድ አሰልጣኝ ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ተገድሎ መገኘቱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



   በደረሰን መረጃ መሰረት ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ገወቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ተገድሎ የተጣለው ዜጋ። የስፖርት አሰልጣኝ መሆኑን ያረጋገጡትን ያካባቢው አርሶአደሮች። በቀጥታ ለፖሊስ  ጥቆማ በመስጠታቸው ምክንያት ማን ተናገሩ አላችሁ በሚል ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን አስረድቷል፣
  ይህ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ገወቻ አካባቢ ተገድሎ የተገኘው አሰልጣኝ። ከትግራይ ክልል ተወዳዳሪዎችን ይዞ የቀረበ ሊሆን እንደሚችል የበርካታዎቹ ግምት ሲሆን የሚመለከታቸው የፖሊስ አባላት ግን መረጃው እንዳይወጣ አጥብቀው እየተቃወሙ መሆናቸውና። የሟቹ አስክሬንም በባህርዳር ከተማ ድባንቂ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን መጋቢት 9/ 2007 ዓ/ም በአካባቢው ነዋሪዎች የቀብር ስነ-ስርዓቱ መፈጸሙ መረጃው አስታውቋል፣
   ከባህር ዳር ሳንወጣ ከዚህ በፊት ተቃውሞ እየተነሳበት የቆየው የመስቀል አደባባይ። በሼህ አላሙዲን አስፈፃሚነት መንገድ ለማስፋት በሚል ከመጋቢት 15/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ በግሪደር እየታረሰ መሆኑንና የአካባቢው ህዝብም ዝምታን መምረጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አመልክቷል፣