Thursday, March 26, 2015

በፀለምት ወረዳ የሚገኙ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ፀረ ህዝብ የፖሊስ አባላት ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ መሆናቸው ታወቀ፣



   ከቦታው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በፀለምት ወረዳ ፍየል ውሃ ቀበሌ የሚኖር ከፍያለው ንጉሴ የተባለ የስርዓቱ የፖሊስ አባል መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓ/ም ከሽረ ወደ ጎንደር በሚያሻግረው የተከዜ ወንዝ ድልድይ ተገድሎ እንደተገኘ ለማወቅ ተችሏል፣
  ይህ እንደዚህ አይነት በስርኣቱ የፖሊስ አባላት ላይ እየተወሰደ ያለ የመግደል እርምጃ የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ በፖሊስ አባሎች የሚፈፀመውን ግፍ መታገስ ባለመቻሉና አቤቱታውን ሰሚ አካል ባለማግኘቱ እየወሰደው ያለው የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን በርካታ ወገኖች እየተናገሩ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣