Tuesday, March 3, 2015

በአማራ ክልል በአንዳንድ ከተሞች የመከላከያ በዓልን አስመልክቶ በህዝብ ዘንድ የተከሰተውን ሽብር መንግስት በበራሪ ወረቀት እያረጋጋ መሆኑ ተገለፀ።



    በክልሉ በባህር ዳር ከተማ በተከበረው  የመከላከያ በዓል  ላይ መነሻውን ጣናን በማካለል በጎርጎራ አድርጎ ከጎንደር እስከ ምዕራብ  ጎጃም መጨረሻ አካባቢ በተደረገ ከ8 በላይ ሄሊኮፕተርና የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎች በመተኮሳቸው ምክንያት በነዋሪው ማህበረሰብ ዘንድ ከባድ ሽብርና አለመረጋጋት መፈጠሩን ተከትሎ መንግስት ራሱ የፈጠረውን የማሸበር ተግባር ለማረጋጋት በሄሊኮፕተር የታገዘ በራሪ ወረቀቶች በመበትንና በየማስታወቂያ ቦርዱ በመለጠፍ ሊያረጋጋው አለመቻሉ ከስፍራው የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
    እንደነዋሪዎች ገለፃ መንግስት በተደጋጋሚ የበተናቸው  የበራሪ ወረቀቶች ፅሁፍ ይዘት “አይዞኣችሁ ምንም ሽብር አልተፈጠረም፤ እየተደረገ ያለው ተኩስ የመከላከያ በዓልን አስመልክቶ የመሳሪያ ፍተሻ እየተደረገ ነው። ለመጨረሻ ጊዜም የካቲት 7 ስለሚደረግ በዚህም እንዳትደናገጡ ” የሚል ማስተባበያ ቢያቀርቡም ህዝቡ ግን መረጋጋት እንዳላሳየ የተገኘ መረጃ አክሎ አስረድተዋል።