Tuesday, March 3, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ-ሰላም ከተማ ዩ.ኤስ.ኤይድ (USAId) በተባለው ድርጅት የቀረበውን መጽሃፍ ለማስተዋወቅ በሚል በተካሄደው ስብሰባ ንትርክ ማጋጠሙን ተገለፀ።



   በአማራ ክልል ከምዕራብ ጎጃም ዞን 15 ወረዳዎች በቋንቋ ከየጉድኝት ማዕከላቱ የተወጣጡ የመምህራን ስብሰባ በፍኖተሰላም ከተማ ዳሞት አዳራሽ ከጥር 23 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የተካሄደው መሆኑን የገለፀው መረጃው በመምህራን ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የመምህር ደመወዝ ከሌሎች የመንግስት ሰራተኞች በእጂጉ ያነሰ ሲሆን የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችና የአበል ክፍያዎችም ዝቅተኛ ናቸው፤ የአንዳንድ ፋውንዴሽንና የአባልነት በሚል ሳንፈልግ የሚወሰደው ገንዘባችን አግባብነት የለውም፤  ለአብነትም ከሽንዲ፤ ከብርሸለቆና  ከቡሬ ወረዳዎች ወደ ስብሰባው  የመጡ መምህራን ከዚህ በፊት የተከፈለንን አበል ለተለያዩ ልማቶች በሚል ተወስዶብናል አሁንም የተስተካከለ አከፋፈል ሊደረግ ይገባል ማለታቸው ታወቀ።
    ከዚህ ጋር ተያይዞ የዞን የትምህርት ፅህፈት ቤት የጉድኝት ማዕከላት ሃላፊዎች ይስተካከላል የሚል ማስተባበያ ቢያቀርቡም ሊቀበሏቸው እንዳልቻሉ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።