Sunday, March 29, 2015

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሃሰት ሪፖርት አሁንም እየቀጠለ ነው



    የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በሚያካሂዱት ስብሰባ። መሬት ላይ ካለው እውነታ ፈፅሞ የማይገናኝና በሬ ወለደ ዓይነት አስገራሚ ሃሰት እያስተጋቡ። የገዛ ህዝባቸውን ሲያደናግሩ መቆየታቸውና አሁንም እየቀጠሉበት መሆኑን ይታወቃል፣
    ሃቀኛ የህዝብ አላማና ራዕይ ሰንቆ። ለሃገር እድገት የሚንቀሳቀስ፤ ድህነትንና ኃላ-ቀርነትን ለማጥፋት ጥረት የሚያደርግ ስርዓት። እታገልለታለሁ በሚለልለት ሃገርና ማህበረሰብ ላይ ውጤቱን የማየቱ ጉዳይ የሚያጠራጥር አይደለም፣ የህዝቡ ማህበራዊ ኑሮ ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የሃገር ሃብት በግለሰቦች እጅ ገብቶ አብዛኛው ህዝብ  በድህነትና ኃላ-ቀርነት የሚሰቃይ ከሆነ ግን። ሺ ግዜ የሃገር እድገት ተረጋግጧል እየተባለ ቢዘመርም። ድምር ውጤቱ ግን ዜሮ ከመሆን አያልፍም፣    
   የትግራይ ክልል መሪዎች ባለፉት መደበኛ ስብሰባዎቻቸው እጅግ ብዙ የሃሰት ሪፖርቶች እያሰሙ መምጣታቸውና አሁንም በ17ኛው መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ በስፋት ሲቀጥሉበት ተስተውሏል፣ ነገር ግን በምክር ቤቱ ውስጥ በአንዳንድ አባላቶች አንደበት የተነሱት ጥያቄዎች የተሟላ መልስ ተሰጥቷቸው የታለፉት ሳይሆኑ። እንደተለመደው። እንሰራዋለን፤ ችግሮች ነበሩን፤ ተጠንተዋል ወ.ዘ.ተ የሚል የቀልድ መልሶች ተሰጥቶባቸው አልፈዋል፣
    ለህዝቡ ብሶትና ችግር ደንታ የማይሰጡት የወቅቱ ሹማምንቶች።  በየአመቱ የሚጠቀሙባቸው የከሰሩ ምክንያቶችን። ዛሬም እንደትናንቱ ሲደጋግሙት ማየት። በህዝቡ ላይ ያላቸውን ንቀት የሚያመላክት ነው፣
የትግራይ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አባይ ወልዱ።  በ17 መደበኛ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በገለጸው የሃሰት ሪፖርት ላይ። የክልሉ እርሻ ከዓመት ወደ ዓመት እድገት እያሳየ ነው፤ እርሻ ላይ ከሚውለው ጠቅላላ መሬት። 51% ከመቶ ለመስኖ ስራ መዋሉን የገለጸበት አስገራሚ የሃሰት ሪፖርት። በአሁኑ ግዜ ደግሞ የእርሻ ስራችን እድገት ማሳየት ያልቻለበት ምክንያት። ማዳበሪያ፤ ምርጥ ዘር፤ ፍግና ኮምፖስ ባለመጠቀማችንና። በዘርፉ ላይ የተሰማሩት የግብርና ባለሙያዎች  በተገቢ መንገድ ክትትል ባለማድረጋቸው ነው ብሎ ሲናገር ተደምጧል፣
   የክልሉ ውሃ ሃብት ሃላፊና የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ከፍተኛ ካድሬ። አለም ገብረዋህድ። ባሁኑ ግዜ በመላው የትግራይ አካባቢ አጋጥሞ ያለውን የውሃ ችግር በምክር ቤቱ አባላት ለቀረበው አቤቱታ። ዛሬም ቢሆን ይሰራል፤ ተጠንቷል፤ እቅድ ተይዞለታል ወ.ዘ.ተ ከሚል ባለፈ ወትሮው ከምናገረው  የተለየ የሰጠው መልስ አልነበረም፣
    የመንገዶችን ስራ በተመለከተም። በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩት መንገዶች በተመደበላቸው ግዜ ያለመፈፀም፤ የተሰሩትም ቢሆን ከጥራታቸው ጀምሮ ግንባታውን የሚቆጣጠሩ አካላት በበጀት ማጠፋፋት ተግባር ላይ የሚያሳዩት ብልሹ አካሄድና እየተሰሩ ያሉ መንገዶችም ለሁሉም ከተሞች የሚያዋስኑ ያለመሆን፤ ቀደም ብለው የተሰሩት መገዶች ከተበላሹ በኋላ የተቀላጠፈ ጥገና ያለማድረግ፤ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ይሰራሉ ተብለው ቃል የተገባላቸውን መንገዶች እንዲሰሩ ያለማድረግ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ወረዳና ቀበሌዎች የሚያገናኝ መንገዶች በመስራት ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩና። ባጠቃላይ ሪፖርት ላይ የሚቀርብና በተግባር መሬት ላይ የሚታየውን እውነታ ፈፅሞ የማይገናኝ መሆኑ። የምክር ቤቱ አባላት በማያሻማ መንገድ ገልፀውታል፣  
     በሌላ በኩል አባይ ወልዱ በተደጋጋሚ አግሮ ኢንዱስትሪን አስመልክቶ ያቀረበው ድንፋታ። የትግራይ አርሶ አደሮች አመቱን ሙሉ ጥረው ግረው ያፈሩት ሰብል በገበያ እጥረት ምክንያት እየከሰሩ። ተበድረው የወሰዱትን የማዳባርያ ዋጋ እንኳን ለመክፈል አቅም አጥተው። በእዳ ምክንያት እንዲታሰሩና ቤተሰባቸውን ጥለው ወደ ስደት የሚያመሩበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው፣
   ባጠቃላይ ሞላው ህዝባችን የስርአቱ በለስልጣናትን ኣስመዘገብነው ከሚሉት የአሃዝ ቀመር ውጭ  በተግባር የተመዘገበ ለውጥ ስለ የለለ  አሁንም ከድህነት መስመር  መውጣት አልቻለም፣