Thursday, March 26, 2015

በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ፓምፕሌቶች በመበተናቸውና። ህዝቡም መልእክቱን በደስታ በመቀበል እያነበበው መሆኑን ተገለጸ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። ይህ በትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/። መጋቢት 12/2007 ዓ/ም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተበተነው ፓምፕሌት በህዝቡ እጅ ደርሶ ለንባብ መብቃቱና። ፓምፕሌቱም ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት የመቐለ ከተማ ውስጥ እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል፣
    በወቅቱ የተበተነውን ፅሁፉ ያነበበው የከተማው ህዝብ። የትህዴን ትግል ፍትሃዊና ወቅታዊ መሆኑንና። በመጪው ግንቦት ወር ላይ የሚደረገው አስመሳይ ምርጫም። ትርጉም እንደማይኖረውና ህዝቡም አማራጩ የትጥቅ ትግል መሆኑን ተረድቶ መነሳት እንዳለበት የሚያመላክት መልእክት የያዘ እንደነበር የገለጸው መረጃው። ፓምፕሌቱ ተሰራጭቶ በሰፊው ህዝብ እጅ መግባቱን ያወቁ የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች ትልቅ ውጥረት ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት። የፖሊስና የደህንነት አባላቶችን በማሰማራት ነዋሪውን ህዝብ እያስፈራሩትና ወደ ስራ ገበታው በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ትልቅ ስጋት እንደሆኑበት መረጃው አክሎ አስረድቷል፣
    ይህ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ያለውን በራሪ ወረቀቶችን የመበተን ስራ። ባለፈው ሁለት ወር ብቻ ሦስት ጊዜ እንደተበተነ ይታወቃል፣