Thursday, March 26, 2015

አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት መጪውን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



በደረሰን መረጃ መሰረት ገዥው አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ንፁሃን ዜጎችን የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር እያሰረ መሆኑን ከገለፁ በኋላ። ከአሸባሪዎች ግንኙነት ፈጥራችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት  ከታሰሩት ወገኖች መካከልም። ተካልኝ ዋሴ የተባለና ለጊዜው ስማቸው ካልታወቁ 3 ጓደኞቹ ጋር መጋቢት 9 ቀን 2007 ዓ/ም  በሑመራ አካባቢ ተንቀሳቅሰው ይሰሩ በነበሩበት ሰዓት በገዥው መንግስት ተላላኪ ደህንነቶች ታፍሰው መታሰራቸውን  አስረድቷል፣
ይህ በእንዲህ እያለ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘም ገዥው መንግስት ፍተሻ ከመጀመሩ በፊት የተደበቀ መሳሪያችሁን አስመዝግቡ በማለት ነዋሪውን ማህበረሰብ እያንገራገረ መሆኑን ምንጮች አስረድተዋል፣ 
    በተጨማሪ በደብረዘይት የወታደራዊ ኢንጂነሪንግ  ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ከ8 በላይ የ4ኛ አመት የኤሮ ስፔስ ሲቪል አቬሽን ዲፓርትመንት  ተማሪዎች ከመጋቢት 7/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ ባልታወቀ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የታገዱ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልከታል፣